የሕክምና ቀጠሮ አስተርጓሚ

ስለዚህ ማስታወቂያ
የሕክምና ቀጠሮ አስተርጓሚ — አማርኛ / እንግሊዝኛ
ዶክተር ወይም ክሊኒክ ቀጠሮ ሲኖርዎት አብሬዎት ሆኜ አስተረጉማለሁ። ሐኪሙ የሚለውን በትክክል እንዲረዱ፣ እርስዎም መጠየቅ የፈለጉትን እንዲጠይቁ እረዳለሁ።
የምረዳባቸው:
- የዶክተር፣ የጥርስ እና የዓይን ቀጠሮዎች
- የላብራቶሪ፣ የኤክስሬይ እና የፋርማሲ ጉብኝቶች
- የሕክምና ቅጾችን መሙላት
- ለኢንሹራንስ ወይም ለክሊኒክ ስልክ መደወል
- የመድኃኒት አወሳሰድ መመሪያን ማስረዳት
እንዴት እንደሚሠራ:
- በአካል አብሬዎት እሄዳለሁ፣ ወይም በስልክ
- በላስ ቬጋስ ሸለቆ ውስጥ በሙሉ
- ቢያንስ 2 ቀን አስቀድመው ቢነግሩኝ ይሻላል
- ዋጋ: ነፃ
የማላደርገው:
- የሕክምና ምክር አልሰጥም። የማስተላልፈው ሐኪሙ ያለውን ብቻ ነው።
- ለሕክምና ውሳኔ ተጠያቂ አይደለሁም።
የሚነጋገሩት ነገር በሙሉ በእኔ ዘንድ ይቆያል።
ዝርዝሮች
- መቼ
- 2026-09-25
- ስንት ሰዓት
- 3
- ቦታ
- Southwest
- እኔ
- አቀርባለሁ
- በየጊዜው የሚደገም
- አዎ