አዲስ ለመጡ ወገኖች በነጻ አግዛለሁ::

About this listing
አዲስ ለመጡ ወገኖች በነጻ አግዛለሁ
ወደ አሜሪካ አዲስ የመጣ ሰው የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ከባድ እንደሆኑ አውቃለሁ። ጊዜዬን ሰጥቼ ለመርዳት ፈቃደኛ ነኝ። ክፍያ የለውም።
የምረዳባቸው:
- ከአየር ማረፊያ መቀበል
- አውቶቡስ እንዴት እንደሚያዝ ማሳየት
- የባንክ ሂሳብ መክፈት
- ስልክና ሲም ካርድ ማውጣት
- ሶሻል ሴኩሪቲ ቢሮ አብሮ መሄድ
- የመንጃ ፈቃድ ወይም መታወቂያ ለማውጣት መመሪያ መስጠት
- ልጆችን ትምህርት ቤት ማስመዝገብ
- ግሮሰሪና ገበያ ማሳየት
- ቅጾችን አብሮ መሙላት
- እንግሊዝኛ ለመለማመድ አብሮ መቀመጥ
ጊዜዬ:
- ቅዳሜና እሁድ / ማታ
- በላስ ቬጋስ
የማላደርገው:
- የኢሚግሬሽን ምክር አልሰጥም። ጠበቃ አይደለሁም።
- ቤት ወይም ሥራ የት መፈለግ እንዳለብዎት አሳይዎታለሁ።
መልእክት ይላኩልኝ። ምን እንደሚያስፈልግዎት ይንገሩኝ።
Details
- When
- 2026-09-23
- I am
- Offering
- This happens regularly
- Yes